የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እና የተማሪዎችን ውጤትለማሳደግ የመምህራን የሙያ ብቃት ምዘና ጠቀሜታው የጎላ መሆኑ ተጠቆመ፡፡

 

የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እና የተማሪዎችን ውጤትለማሳደግ የመምህራን የሙያ ብቃት ምዘና ጠቀሜታው የጎላ መሆኑ ተጠቆመ፡፡

(መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም) የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዛሬ ከ10ሺ በላይ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮችን የሙያ ብቃት ምዘና አካሂደዋል፡፡

በሙያ ብቃት ምዘናው ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ እንደገለፁት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የመምህራን አቅም በየግዜው መጎልበት ያለበት በመሆኑ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች በሚያስተምሩበት የትምህርት ይዘት የሙያ ብቃት ምዘና መውሰድ ተገቢ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በሙያ ብቃቱ ምዘናውን ያላለፍ ተመዛኞች በቀጣይ ያላቸውን ክፍተት እና ጉድለት በመለየት ስልጠና የሚሰጣቸው እና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ይደረጋል ብለዋል፡፡

e t m
a b  

በተጨማሪም በየግዜው የሚሰጠው የሙያ ብቃት ምዘና ስርዓት የተመዛኞች ቁጥሩ እየጨመረ የሄደበት አግባብ ያለ ሲሆን የማለፍ ምጣኔውም እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኢዘዲን ሙስባህ እንደገለጹት በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ትልቅ ሚና ያላቸው መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች በመሆናቸው በየግዜው ብቃታቸውና እውቀታቸውን እንዲሁም የማስተማር ስነ ዘዴ መረጋገጥ እንዳለበት አሳውቀዋል፡፡ በመሆኑም ባለስልጣኑ ከሚመለከታቸው አከላት ጋር በመሆን ምዘናው በተገቢው መልክ እንዲካሄድ የባለፈውን አመት ምዘና ሂደት በመገምገም እና ለመምህራን ግንዛቤዎችን በመፍጠር ቅድመ ዝግጅቶች በማድረግ ምዘናው መከናወኑን ተናግረዋል፡፡

በዚህም በዛሬው ዕለት 10,121 መምህራን እና ርዕሰ መምህራን በ44 የትምህርት አይነቶች ቅድሚያ የሚጠበቅባቸውን መስፈርት በማሞላት የሙያ ብቃት ምዘናው መውሰዳቸውን አሳውቀዋል፡፡

የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክተል ስራ አስኪያጅ አቶ አለልኝ ወንዴ በበኩላቸው እንደገለጹት ምዘናው ለአገር ግንባታ እና ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ጠቃሚ መሆኑን ጠቅሰው መምህራን በራሳቸው ፍላጎት በመመዝገብ ምዘናውን የሚወስዱበት አግባብ በመኖሩ በየግዜው ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣ ሲሆን በዘንድሮ አመትም ምዘናው በሁሉም ክፍለ ከተማ በተመረጡ 12 የሚዘና ጣቢያ 124 ሱፐርቫይዘሮች ፣ 376መዛኞች እንዲሁም 98 አስተባባሪዎችና 81 የአይነስውራን አንባቢዎች መመደባቸውን አስረድተዋል።

ምዘናውን የወሰዱ አንዳንድ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች በሰጡት አስተያየት ምዘናው ከሚያስተምሩት ትምህርት ጋር ተያያዥነት ያለው ߹ራሳቸውን እውቀት የገመገሙበት ߹ እንዲሁም የተማሪ ውጤት እና ስነ ምግባር ለማሻሻል እና ለቀጣይ ስራቸው ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ጠቅሰው ሌሎችም በምዘና ስራአቱ ላይ አንዲያልፍ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡