|
|
|
|
የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የአሰራርና ተጠያቂነት ረቂቅ መመሪያ ላይ ተወያየ፡፡
መጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በትምህርት ተቋማት ውስጥ ግልጽ የአሰራርና የተጠያቂነት ስርዓት ለመዘርጋት የሚያስችሉ የደንብና መመሪያ ረቂቆችን ከጠቅላላ ካውንስሉ ጋር ገመገመ።
ባለስልጣኑ ግምገማውን ያካሄደው በአሰራርና ተጠያቂነትን ለማስፈን በወጣ ደንብ እና በትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጥ ረቂቅ መመሪያ ላይ ትኩረት በማድረግ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
በእለቱም የመነሻ ሰነዶችን ያቀረቡት የባለስልጣኑ የልደታ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ዘመነ አብይ አለማውን እንደገለጹት የትምህርትና ስልጠና ጥራትን ማረጋገጥ እና የሙያ ብቃትና የትምህርት አሰጣጥ ተገቢነትን መቆጣጠር እንዲሁም በዘርፉ ጠንካራ የአሰራርና የተጠያቂነት ስርዓት ለመዘርጋት እደሆነ ገልጸዋል።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኢዘዲን ሙስባህ በበኩላቸው ረቂቅ መመሪያዎቹ ተቋሙ የጀመረውን የሪፎርም ስራ ለማገዝ እና በትምህርት ጥራት ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በህግ ማዕቀፍ ለመፍታት ትልቅ ፋይዳ እንዳላቸው ገልጸዋል።
በውይይቱ ላይ የጠቅላላ ካውንስሉ አባላት በረቂቅ ሰነዶቹ ላይ ዝርዝር ውይይት ካደረጉ በኋላ ግብዓቶች ታክለውባቸው ለቀጣይ በባለድርሻ አካላት ውይይት እንዲደረግባቸው አቅጣጫ ተቀምጧል።