በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተከናወነ፡፡

ሚያዚያ 14 ቀን 2016 ዓ.ም

3 2

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የ2016 በጀት ዓመት አገልግሎት አሰጣጥ ያለበት ነባራዊ ሁኔታዎች በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ በመርሃ-ግብሩ ላይ እንደተናገሩት የውይይት መድረኩ አላማ ባለስልጣኑ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር በማድረግ የሚታዩ ችግሮችን በአፋጣኝ ለመፍታት የሚያስችል እንደሆነ ገልጸው፤በባለስልጣኑ የሚሰጡ አገልግሎቶች ከቅልጥፍና እና ውጤታማነት አንጻር ያለውን ችግር በመቅረፍ ተቋማዊ ለውጥን በማምጣት የተገልጋዩን እርካታ ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ አድማሱ ደቻሳ በበኩላቸው እንደተናገሩት የምንሰራው ለትውልድ በመሆኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለንን ግንኙነት አጠናክረን በመቀጠል ፤ተቋማት ወደ ስታንዳርድ መጥተው ስራዎችን በጋራ ወደተሻለ ደረጃ ማድረስ አስፈላጊና ተገቢ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

1


በትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ታደለ የመወያያ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በዚህም አገልግሎትን ውጤታማ ለማድረግ የተቋማት ሚና ፣የዜጎች ስምምነት ሰነድ ትግበራ፣ከመሰረታዊ ስራ ሂደት ትግበራ አንጻር፣የመረጃ ግልጽነትን ማረጋገጥ፣የተገልጋይ እና ባለድርሻ አካላትን ማሳተፍ ፣አሰራርንና ውጤታማነትን በጥናት መፈተሽ፣የአደጃጀቶች ሚና፣የባለ ድርሻ አካላት ተሳትፎ በሚሉና በሌሎችም ዝርዝር ሃሳቦችን በማንሳት ለውይይት አቅርበዋል፡፡

4


በመድረኩም የባለስልጣኑ አገልግሎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ እንደመጣና የተገልጋዩም እርካት እየጨመረ መሆኑን በመድረኩ የተገኙት ከአጠቃላይ ትምህርትና ከቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ያነሱ ሲሆን ሰፊ ውይይትም ተደርጎበታል፡፡