ለእውቅና ፍቃድ እድሳት ውጤታማነት የባለሙያዎች ኃላፊነት

የትምህርትና ስልጠና ተቋማት እውቅና ፈቃድ እድሳትና ምዘና ዳይሬክቶሬት ከግል የትምህርት ተቋማት እና ከዳይሬክቶሬቱ ባለሙያዎች ጋር ውይይት አደረገ፡፡

በውይይቱም ላይም በ2011ዓ.ም እውቅና ፈቃድ እድሳት እንዴት እንደ ተካሄደ የነበሩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች የሚገልጽ ሰነድ ቀርቧል፡፡

ሰነዱን ያቀረቡት የዳይሬክቶሬቱ የቡድን መሪ የሆኑት ወ/ሮ ሜሮን  ጋሹ እንደገለጹት  የትምህርት ተቋማቱ ከግብዓትና አደረጃጀት አንፃር ያላቸውን ጠንካራና ደካማ ጎኖች በመለየት በእያንዳንዱ የትኩረት ነጥብ መሠረት ያደረገ የቃልና የጹሑፍ ግብረ መልስ በመስጠት እንዲሁም ለተግባራዊነቱ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ሲሰራ  መቆየቱን አሳውቀዋል፡፡

p1 1 p2 3

የሰነዱ አላማ 2011 ዓ.ም የእውቅና ፍቃድ እድሳት ሂደት የነበሩትን ደካማ ጎኖች በማረም በቅርቡ ለሚከናወነው የዕውቅና ፍቃድ እድሳት ላይ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በአግባቡ እንዲሰሩ ለማስቻል እንዲሁም ተቋማት የሚጠበቅባቸውን ስታንዳርድ መሰረት በማድረግ ት/ቤቶቻቸውን በማደራጀት በትምህርት ጥራት እና ተገቢነት ላይ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ለማስገንዘብ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዕለቱ የተሻሻለው የእውቅና ፍቃድ እድሳት መመሪያ እና የባለስልጣኑ ኃላፊነት እና ተግባር የሚገልጽ ሰነድ ቀርቧል፡፡

በቀረቡት የሰነድ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ ውይይት ተካሂዶል ፤ተሳታፊዎቹም ለትምህርት ስራው እንቅፋት የሆኑባቸውን የተለያዩ ጥያቄዎች እና ሃሳቦች አቅርበዋል፡፡

p3 2 p4 2

የትምህርትና ስልጠና ጥራት፣ሙያ ብቃትና ምዘና ማረጋገጫ ባለስልጣን ምክትል ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ወ/ሮ ፍቅርተ አበራ በማጠቃለያ ንግግራቸው እንደገለፁት በቀጣይ በሚከናወነው የዕውቅና ፍቃድ አሰጣጥ ሂደት ላይ ያልተገባ የዕውቅና ፍቃድ ለማግኘት የሚሞክሩ ተቋማት እና የሥራ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ በማይወጡ ባለሙያዎች ላይ የተጠያቂነት ስርዓት በማስፈን ተግባራዊ እንደሚደረግ የጠቆሙ ሲሆን

ተቋማት በቀጣይ የትምህርት ዘመን ከወዲሁ ያሉባቸውን ክፍተቶች በመሙላት እና በአገራችን የተቀረፀውን ስርዓተ ትምህርት በአግባቡ በመተግበር ለትምህርት ጥራት መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡

በዕለቱ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ከ500 በላይ ተሳታፊዎች በውይይቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡

p10 p11

                                         ዘገባው የባለስልጣኑ ሕዝብ ግንኙነት ቡድን